የጤና መሠረተ ልማት ውስንነት ካልሆነ በቀር "የኢትዮጵያ ሐኪሞች ከዚህም በላይ ይችላሉ!"- ኢትዮጵያዊው ዶክተር
19:24 10.07.2025 (የተሻሻለ: 19:34 10.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየጤና መሠረተ ልማት ውስንነት ካልሆነ በቀር "የኢትዮጵያ ሐኪሞች ከዚህም በላይ ይችላሉ!"- ኢትዮጵያዊው ዶክተር

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የጤና መሠረተ ልማት ውስንነት ካልሆነ በቀር "የኢትዮጵያ ሐኪሞች ከዚህም በላይ ይችላሉ!"- ኢትዮጵያዊው ዶክተር
ከሰሞኑ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተጣብቀው የተወለዱ ህጻናትን የመለየት ቀዶ ጥገና በስኬት አከናውኗል።
በሆስፒታሉ ታሪክ በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነው እና ከ3 ሰዓት በላይ የወሰደውን ህይወት የማዳን ትንቅንቅ አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ ቃለምልልስ የሰጡት ዶ/ር ዓባይ ጎሳዬ አንደኛው ጨቅላ ሙሉ የሰውነት ክፍል ሲኖረው፤ የአፈጣጠር ችግር ያለበት መንትያው ግን ጥቂት ያልጎለበቱ የሰውነት ክፍሎችን ብቻ ይዞ እንደተወለደ ነግረውናል፡፡
ሐኪሞቹ የሰውነት አካል ጥናት ዕውቀታቸውን ከቀዶ ጥገና በፊት ከተደረጉ ምርመራዎች ጋር በጥንቃቄ አመሳክረው መንትዮቹን ለያይተዋል።
ከቀዶ ጥገናው በኋላ ሙሉ አካል ያለው ህጻን በተረጋጋ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ዶ/ር ዓባይ ጎሳዬ ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X