- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

የአፍሪካ የመጪው ዘመን ድል፦ የሥራ ፈጠራ ለወጣቶች እና የግብርና አቢዮት

የአፍሪካ የመጪው ዘመን ድል፦ የሥራ ፈጠራ ለወጣቶች እና የግብርና አቢዮት
ሰብስክራይብ
በአፍሪካ ሰፊ የህዝብ ቁጥር የሚይዘው ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል ከሥራ አጥነት ለማላቀቅ መንግስታት አዳዲስ የሥራ ፈጠራዎችን ሊያበረታቱ እንደሚገባ ይታመናል።
ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ስለአፍሪካ አህጉር የሥራ ፈጠራ እና የሀገራት የጋራ ቅንጅት በጥልቀት ለመወያየት የኢትዮጵያ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል አህመድን ጨምሮ ሌሎች የአህጉሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 2 በተካሄደው በ3ኛው የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ጉባኤ ላይ አነጋግሯቸዋል።
አፍሪካ ከፍተኛ ሀብት እና አቅሟ የሆነውን ወጣቱን ኃይል እና የግብርናው ዘርፍ በማቀናጀት የለውጥ ጎዞዋን ማቀጣጠል ይቻላታል፡፡
''አፍሪካ ካላት አቅም አንዱ የግብርናው ዘርፍ ነው። ስለዚህ ዘርፉን በማሻሻል [...] በአህጉሪቱ የተለያየ የምጣኔ ሐብት እንቅስቃሴ ውስጥ የግብርናውን ዘርፍ ለወጣቶች የሥራ ዕድልና ፈጠራና ምቹ የዕድገት መስክ ሊሆን ይችላል'' ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ተናግረዋል።
የጋና የሥራና ሠራተኞች ሚኒስትር ራሺድ ፔልፒዩ (ዶ/ር) በበኩላቸው፦
በአህጉሪቱ ያሉ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በተመለከተ  "በአፍሪካ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ኢኮኖሚውን እየመሩት ነው፣ እንዴት ማጎልበት፣ ማሳደግ ፣ ማስፋፋት እንደምንችል ለመረዳት በቅድሚያ እንዴት አድርገን እንደምንጠቀም ማየት ያስፈልጋል። ስለዚህ ኢንቨስትመንቱን የሚያሰፋና የወጣቶችን ሥራ አጥነት ችግር ለመፍታት የመንግሥት የኢኮኖሚ ልማት በቂ አለመሆኑን ካወቅን ፈጠራ እና ኢንቨስት ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን፤'' ሲሉ ተናግረዋል።
ስለ 3ኛው የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ጉባኤ፣ በአፍሪካ የወጣቶችን ሥራ አጥነት ለመቅረፍ መንግስታት ስለሚወስዷቸው እርምጃዎች፣ የእርስ በርስ ትብብርና ቅንጅት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች የበለጠ ለመገንዘብ ይህን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን የሶቨርኒቲ ሶርስ ፕሮግራም እንዲከታተሉ ጋብዘንዎታል።
አዳዲስ ዜናዎች
0