መንግሥት የታዳሽ ኃይል የብድር ሥርዓት ሊጀምር ይገባል ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ
16:50 10.07.2025 (የተሻሻለ: 16:54 10.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
መንግሥት የታዳሽ ኃይል የብድር ሥርዓት ሊጀምር ይገባል ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ
የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት 93 ሚሊየን በላይ ዜጎችን የንፁህ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ ያነገበው እቅድ የገጠሩን ማሕበርሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምርምር እና ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ጌታቸው አዳሙ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ሆኖም መሳሪዎቹ በጣም ውድ በመሆናቸው የሕብረተሰቡን ኪስ ሊፈታተኑ እንደሚችሉ ነው ባለሙያው ያብራሩት፡፡
“መንግሥት የታዳሽ ኃይል የብድር ሥርዓት መጀመር አለበት፡፡ ይሕም እቅዱን ወዲያው ለመተግበር እና ተጨማሪ ሥራ ለመፍጠር እንዲሁም አነስተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ኢንዱስትሪዎችን መፍጠር ያስችላል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አክለውም ሀገሪቱ ከታዳሽ ኃይሎች የምታመነጨውን ኃይል ለመጨመር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ መሆኗን አብራርተዋል።
"... የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገሪቱ ያለውን የፀሐይ ኃይል አጠቃቀም ለማስፋት የፀሐይ ኃይል ማምረቻ ሴሎችን የሚገጣጥሙ እና ፓነሎችን የሚሠሩ ኢንዱስትሪዎችን ለመፍጠር አቅዷል" ብለዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X