የጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በኤም ፖክስ ተይዘው የነበሩ ስዎች ሙሉ በሙሉ ማገገማቸውን አስታወቀ
14:21 10.07.2025 (የተሻሻለ: 14:24 10.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በኤም ፖክስ ተይዘው የነበሩ ስዎች ሙሉ በሙሉ ማገገማቸውን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በኤም ፖክስ ተይዘው የነበሩ ስዎች ሙሉ በሙሉ ማገገማቸውን አስታወቀ
ሚንስቴሩ ግንቦት 16 በበሽታው የተያዘ የመጀመሪያውን ታማሚ መገኘቱን ይፋ ካደረገ በኋላ እስከ ሐምሌ 2 ድረስ ለ520 በበሽታው ለተጠረጠሩ ሰዎች የላብራቶሪ ምርምራ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበሽታው ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ያነሷቸው ነጥቦች፦
በምርመራው 26 ሰዎች በሽታው እንደተያዙ ተረጋግጧል፣
አንድ ታማሚ በበሽታው ህይወቱ አልፏል፣
ቀሪዎቹ 25 ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ ከበሽታው አገግመዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ህብረተሰቡ ለበሽታው አጋላጭ ከሆኑ መንገዶች በመጠንቀቅ እና የመከላከያ መንገዶችን ችላ ሳይል በመተግበር የበሽታውን ስርጭት በዘላቂነት እንዲገታ ጥሪ አቅርቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X