የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ100 የሙያና ቴክኒክ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የስታርትአፕ ድጋፍ ማዕከላትን ሊያቋቋም እንደሆነ አስታወቀ
12:37 10.07.2025 (የተሻሻለ: 12:44 10.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ100 የሙያና ቴክኒክ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የስታርትአፕ ድጋፍ ማዕከላትን ሊያቋቋም እንደሆነ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ100 የሙያና ቴክኒክ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የስታርትአፕ ድጋፍ ማዕከላትን ሊያቋቋም እንደሆነ አስታወቀ
እነዚህ ማዕከላት ለሥራ ፈጣሪዎች የንግድ ሥልጠና፣ ማማከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ እና የስኬት እድላቸውን ሊጨምሩ የሚችሉ ግንኙነቶችን ጨምሮ ወሳኝ ድጋፍ ለመስጠት ያለሙ ናቸው ተብሏል፡፡
“ኢትዮጵያ የፈጠራ ሃሳቦች እጥረት የለባትም፤ ነገር ግን ስታርትአፖች ብዙውን ጊዜ በገንዘብ እጥረት፣ በቢሮክራሲያዊ እንቅፋቶች እና በባለድርሻ አካላት መካከል ባለው ደካማ ቅንጅት ይጎዳሉ” ሲሉ በሚኒስቴሩ የሥራ ፈጣራ ክፍል ኃላፊ ብርሃኑ አደሬ ለሀገር ውስጥ ጋዜጣ ተናግረዋል።
ኃላፊው ሥራ ፈጣሪዎች የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች ለመቅረፍ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ እና አዳዲስ የፋይናንስ አማራጮችን የሚያስተዋውቅ ረቂቅ የስታርትአፕ ልማት ፖሊሲ እየተጠናቀቀ መሆኑንም ገልፀዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X