- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

አፍሪካ የቱሪዝም አቅምን መክፈት፡- ዕድሎችን ማሰስ እና እንቅፋቶችን ማለፍ

አፍሪካ የቱሪዝም አቅምን መክፈት፡- ዕድሎችን ማሰስ እና እንቅፋቶችን ማለፍ
ሰብስክራይብ
አፍሪካ አስደናቂ መልክዓ ምድር፣ የበለጸገ ባህል እና በፍጥነት እያደገ ያለው የዲጂታል ገጽታ በዓለም ቱሪዝም ውስጥ ያንቀላፋው ዘርፍ አድርጎት ቆይቷል።
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ክፍል፣ ስለዚሁ የአፍሪካ ያልተነካው ዘርፍ በስፋት እንዳስሳለን፡፡
ይህንን ያልተነካ እምቅ ሀብትም ከታላቅ ኢትዮጵያ አስጎብኚዎች ማኅበር መስራች ናሆም አድማሱ ጋር በመሆን እንመረምራለን።
ከሥነ-ምህዳር ቱሪዝም እስከ ጂኦፓርኮች፣ አፍሪካ ለውጥ የመፈጠር መንገድ ላይ ነች — ነገር ግን እንቅፋቶችም አሉ፤ በቅጡ ያልለሙ መሠረተ ልማቶች፣ የደህንነት ስጋቶች እና በቂ ያለሆነው ኢንቨስትመንት ዘርፎን ወደኋላ ጎትተው ይዘዉታል።
ናሆም ስለአንድነት ባነሳው ሃሳብ፡- “አፍሪካን እንደ ነጣጥለን ሳይሆን አእንደ አንድ[ጥቅል] መዳረሻ  መሸጥ እንችላለን። […] [የእያንዳንዱን ሀገር] ልዩነትን ከፍ በማድረግ እና አብረን በመስራት አፍሪካን እንደ አንድ መድረሻ መሸጥ እንችላለን”፣ ብሏል።
ይህ የመዳረሻነት ገበያም ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት የብሪክስ ጥምረት ከፍተኛ አቅም የመሆን ዕድሉም ሰፊ ነው።
“በ ብሪክስ ውስጥ [ያለው]... የኢኮኖሚ ኃይል እና ታሪካዊ ግንኙነቶች ለቱሪዝም ሊወል ይችላል።” ሲል የታላቅ ኢትዮጵያ አስጎብኚዎች ማኅበር መስራች ናሆም አድማሱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡
የአፍሪካ የቱሪዝም የወደፊት ዕጣ እንዴት እየተገነባ እንደሆነ እና የአፍሪካን የጂኦፓርኮች የተነሱ ህሳቦችን ይበልጥ ለመረዳት ይህን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን የራይዚንግ ሳውዝ ክፍል ያዳምጡ።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify
አዳዲስ ዜናዎች
0