የቡና ዘርፉን ለማሳደግ ያለመ ብሔራዊ የቡና ባለድርሻ አካላት አስተባባሪ ኮሚቴ ሥራ ጀመረ
19:38 09.07.2025 (የተሻሻለ: 19:44 09.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቡና ዘርፉን ለማሳደግ ያለመ ብሔራዊ የቡና ባለድርሻ አካላት አስተባባሪ ኮሚቴ ሥራ ጀመረ
ኮሚቴው በህዳር ወር የተዋወቀውን ብሔራዊ የቡና መድረክ ለዘርፉ የወደፊት እድገት የመምራት ኃላፊነት እንደተጣለበት ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኮሚቴው ሰብሰቢ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው የኢትዮጵያ ቡና ዘርፍ ያሉበትን ተግዳሮቶች ዘርዝረዋል፦
🟠 የአየር ንብረት ለውጥ፣
🟠 የገበያ ተጋላጭነት እና
🟠 የቁጥጥር እንቅፋቶች።
የኢትዮጵያ የቡና ዘርፍ 5 ሚሊየን አነስተኛ አርሶ አደሮችን፤ አብዛኞቹ ሴቶችን እንደሚደግፍ እና ሩብ ለሚጠጋ የሀገሪቱ ሕዝብ በቀጥተኛ እና በተዘዋዋሪ መንገድ የሥራ ዕድል እንደፈጠረ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ግዜ ከቡና የወጪ ንግድ 2.6 ቢሊየን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ሰብስባለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X