የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር በወታደራዊ መንገድ አይቆምም ሲሉ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አስታወቁ
18:34 09.07.2025 (የተሻሻለ: 18:44 09.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር በወታደራዊ መንገድ አይቆምም ሲሉ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር በወታደራዊ መንገድ አይቆምም ሲሉ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አስታወቁ
ራፋኤል ግሮሲ ኢራን በትልቅነቷ፣ በጠንካራ ኢኮኖሚዋ፣ በኢንዱስትሪ አቅሟ እና በቴክኒካል ብቃቷ ምክንያት በወታደራዊ መንገድ ልትገታ የማትችል ሀገር ናት ሲሉ ገልጸዋታል፡፡
▪ ግሮሲ የኒውክሌር ጉዳይ በኃይል ሊፈታ እንደማይችል አጽንኦት በመስጠት፤ መፍታት የሚቻለው ጥብቅ የማረጋገጫ ሥርዓትን በሚያረጋግጥ ሁሉን አቀፍ ስምምነት ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፈው ሰኔ እስራኤል ጥቃት ከመሰንዘሯ በፊት የተመድ የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ባወጣው ሪፖርት ኢራን የተለያዩ ከኒውክሌር ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎቿን እያሳወቀች አይደለም ሲል ከሷል፡፡
▪ይህ በእንዲህ እንዳለ ግሮሲ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳላት የሚያሳይ እርግጠኛ ማስረጃ እንደሌለ ገልፀው፤ ቦምብ የመሥራት አቅምን የሚጠቁሙ ምልክቶች እንዳሉ አንስተዋል።
▪አይኤኢኤ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመሥራት የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን እንዳልወሰደች ግን ያምናል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X