"እኛ ብሪክስ ውስጥ የምንገኘው ለማገልገል አይደለም" ሲሉ አፍሪካ በድኑ ውስጥ ያላትን ሚና የጋናው የሥራ ሚኒስትር ተናገሩ

ሰብስክራይብ

"እኛ ብሪክስ ውስጥ የምንገኘው ለማገልገል አይደለም" ሲሉ አፍሪካ በድኑ ውስጥ ያላትን ሚና የጋናው የሥራ ሚኒስትር ተናገሩ

"የሆነ አካል አፍሪካን መደገፍ አለበት የሚለው አስተሳሰብ መቆም አለበት። አብረን መሥራት አለብን፤ እኛ ባልደረቦች ነን። እኛ ሉዓላዊ መብት ያለን ሉዓላዊ ሀገራት ነን" ሲሉ ሚኒስትሩ ራሺድ ፔልፑኦ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

አክለውም አፍሪካ በዓለም አቀፍ ትብብሮች ውስጥ ያላትን ትክክለኛ ቦታ አጽንዖት ሰጥተው አንስተዋል።

"ብሪክስ ውስጥ ያሉ ሀገራት ዕድገታቸውን ፈልገው እኩል አጋሮች ሆነው በመሥራት ላይ ይገኛሉ" ሲሉ ፔልፑኦ አዲስ አበባ ከተካሄደው 3ኛው የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ መድረክ ጎን ለጎን ተናግረዋል።

አፍሪካ ከቀሪው ዓለም ጋር በእኩልነት ለመጓዝ ምን መለወጥ አለበት? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ከላይ ያለውን ቪዲዮ ይመልከቱ።

በቃለመጠይቁ ፔልፑኦ አፍሪካ መፍጠር የምትችለውን ነገር መለመን እንድታቆም አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0