ኢትዮጵያ የራሷን የዋትስአፕ፣ ጂሜይል እና ዙም ስሪቶች እያበለፀገች እንደሆነ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የራሷን የዋትስአፕ፣ ጂሜይል እና ዙም ስሪቶች እያበለፀገች እንደሆነ ተገለፀ
ኢትዮጵያ የራሷን የዋትስአፕ፣ ጂሜይል እና ዙም ስሪቶች እያበለፀገች እንደሆነ ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.07.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የራሷን የዋትስአፕ፣ ጂሜይል እና ዙም ስሪቶች እያበለፀገች እንደሆነ ተገለፀ

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አማካኝነት የተገነቡት የዲጂታል ቴክኖሎጂ መድረኮች የሳይበር ደህንነትን ለማሻሻል እና ከኢትዮጵያ የቁጥጥር ማዕቀፍ ውጪ በሆኑ የውጭ ኩባንያዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ የታለሙ እንደሆኑ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ለጂሜል አማራጭ ሆኖ የቀረበው “እርጋሜል” ከወዲሁ በመንግሥት ተቋማት ሥራ ላይ መዋል እንደጀመረ ተነግሯል፡፡ "ሰርኩትኒ" የዋትስአፕ እና ቴሌግራም ምትክ እንዲሆን የሚጠበቅ ሲሆን ገና በትግብራ ላይ ነው የሚገኘው፡፡

ለቨርቹዋል ግኑኝነቶች እንዲሆን በኢንሳ የበለፀገው “ደቦ” ደግሞ የሙከራ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ውጪ ሠር ሶፍትዊሮችን ከመንግሥት አገልግሎት የሚያስወጡ ተጨማሪ የዲጂታል መፍትሄዎችን እያጎለበተ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0