የኢትዮጵያን ቱሪዝም ለማሳደግ ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ማዘመን እንደሚገባ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታው ተናገሩ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያን ቱሪዝም ለማሳደግ ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ማዘመን እንደሚገባ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታው ተናገሩ

የቱሪዝም ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው የቪዚት ኢትዮጵያ የዲጂታል ፕላትፎርም የሀገሪቱን ቱሪዝም ለማስተዋወቅ፣ የአገልግሎት ጥራት እና ታማኝነትን ለማሻሻል ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥርም ሚኒስትር ዴዔታው ዶ/ር እንደገና አበበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

"ቱሪዝም በመንግሥት ቢመራም፤ ዘርፉ በዋነኛነት የሚያንቀሳቀሰው በግሉ ዘርፍ ነው። ስለዚህ እነዚህን ሁሉ ነገሮች በአንድ መድረክ መሰብሰብ ይኖርብናል። መሠረተ ልማታችንን፣ የክፍያ ስርዓቱን እንዲሁም ከቱሪዝም ዘርፉ ጋር የሚጣመሩ ሌሎች ስርዓቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ ይጠበቅብናል" ብለዋል።

የቪዚት ኢትዮጵያ ዲጂታል ፕላትፎርም በቱሪዝም ዘርፍ በኩል ኢትዮጵያን ዲጂታላይዝ የማድረግ ሥራ አንዱ ማሳያ መሆኑንም አመላክተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0