የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣናቸውን የማጣት ስጋት ውስጥ በመሆናቸው "ተቃዋሚዎችን ከፖለቲካው መድረክ እያስወገዱ ነው" ሲሉ ምሁሩ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣናቸውን የማጣት ስጋት ውስጥ በመሆናቸው "ተቃዋሚዎችን ከፖለቲካው መድረክ እያስወገዱ ነው" ሲሉ ምሁሩ ተናገሩ
የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣናቸውን የማጣት ስጋት ውስጥ በመሆናቸው ተቃዋሚዎችን ከፖለቲካው መድረክ እያስወገዱ ነው ሲሉ ምሁሩ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.07.2025
ሰብስክራይብ

የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣናቸውን የማጣት ስጋት ውስጥ በመሆናቸው "ተቃዋሚዎችን ከፖለቲካው መድረክ እያስወገዱ ነው" ሲሉ ምሁሩ ተናገሩ

አርሜኒያዊው ነጋዴ ሳምቬል ካራፔትያን በጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን መንግሥት ጫና ከገጠማቸው ቀዳሚ ሰው ቢሆኑም የመጨረሻው ግን አይደሉም ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ ሴምዮን ባግዳሳሮቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ባግዳሳሮቭ በትናትናው ዕለት በካራፔትያን ባለቤትነት ስር በሚገኘው የኤሌክትሪክ ኔትወርኮች ኦፍ አርሜኒያ ኩባንያ ላይ ፖሊስ ያካሄደውን ወረራ በተመለከት አስተያየታቸውን ሲሰጡ “ፓሺንያን ሁሉንም ነገር መውረስ ይፈልጋሉ። ነገ የሩሲያ ንብረት የሆነው የአርሜኒያ ምድር ባቡር ወይም ሌላ ነገር ቢወረስ አይግረማችሁ” ብለዋል።

ምሁሩ አክለውም የመንግሥት እርምጃ ፓሺንያን ወደ አውሮፓ ኅብረት ለመግባት ከሚያደርጉት ጥረት ጋር የተገናኘ ነው ይላሉ።

“እንደ ካራፔትያን ያሉ ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎችን ማሰር የአውሮፓን ኅብረት ያስደስታል፤ ይህ ደግሞ ፓሺንያን ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማቋረጥ እያደርጉት ያለው ጥረት አካል ነው” ሲሉ ባግዳሳሮቭ አስረድተዋል።

በመንግሥት እና በአርሜኒያ ሐዋርያዊ ቤተ-ክርስቲያን መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ቤተክርስቲያኗን ደግፈው የቆሙት ካራፔትያን፤ ሰኔ 10 ቀን ሥልጣን በኃይል ለመንጠቅ በማነሳሳት ተወንጅለው ለሁለት ወራት እስር ቢፈረድባቸውም፤ እሳቸው ግን ግን ክሱን አስተባብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0