“አሜሪካ በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያላትን የበላይነት አላግባብ እየተጠቀመችበት ነው" - ኢትዮጵያዊው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ“አሜሪካ በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያላትን የበላይነት አላግባብ እየተጠቀመችበት ነው" - ኢትዮጵያዊው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ
“አሜሪካ በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያላትን የበላይነት አላግባብ እየተጠቀመችበት ነው - ኢትዮጵያዊው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.07.2025
ሰብስክራይብ

“አሜሪካ በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያላትን የበላይነት አላግባብ እየተጠቀመችበት ነው" - ኢትዮጵያዊው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

የብሬተን ዉድስ ተቋማት (አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ) በቡድን 7 ሥር ያሉ፤ የበድኑን አባል ሀገራት ዓለማ የሚያስፈፅሙ ናቸው የሚሉት ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር)፤ የብሪክስ ሀገራት የምዕራቡ ዓለም የዘረጋውን አግላይ ስርዓት ለመለወጥ የሚችሉበት አቋም ላይ እንደሚገኙ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ጠቁመዋል።

"ዩናይትድ ስቴትስ አሁን ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች የዓለም የንግድ ድርጅትንም መነካካት ጀምራለች። ስለዚህም ብሪክስ የራሱን የዓለም የንግድ ድርጅት ያቋቋማል።...አዲሱ የልማት ባንክ ለብሪክስ ሀገራት ዕድገት የስበት ማዕከል ይሆናል። እነዚህ ሁሉ ጉዳዮች ብሪክስ የአሜሪካን ወይም የምዕራቡን ዓለም የኢኮኖሚ የበላይነት ለመፈታተን ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ" ብለዋል።

በሪዮ ዴጄኔሮ የብሪክስ መግለጫ ራሱን የቻለ የክፍያ ስርዓት እንዲዘረጋ ምክረ ሃሳብ መቀመጡንም ተናግረዋል።

"...ከአንቀፅ ቁጥር 42 እስከ 80፤ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ንግድ እና የፋይናንስ ትብብርን ስለማጠናከር ይናገራል። ይህ የመጣው የአሜሪካ መንግሥት በፕሬዝዳንት ትራምፕ አማካኝነት እያንዳንዱ የዓለም ሀገር ላይ ከፍተኛ ታሪፍ በሚጥልበት ወቅት ነው። ብሪክስንም ዶላርን በመገበያያነት የማይጠቀም ከሆነ አስፈራርተዋል" ሲሉ አስታውሰዋል።

ለዚህ የብሪክስ ሀገራት እየተዘጋጁ እንደሆነ ባለሙያው አንስተዋል።

"የመጀመሪያው ጉዳይ የፋይናንስ ተነባቢነታቸው ነው። ሌላው የራሳቸውን መገበያያ መፍጠራቸው ነው፡፡ ዋናው ነገር ግን አሁን በየሀገራቱ ገንዝብ ግብይት ለመፍጠር እየሠሩ መሆናቸው ነው” ብለዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0