ብሪክስ ትራምፕ ችላ ሊሉት የማይችሉት የሀገራት ስብስብ እንደሆነ ባለሙያው ተናገሩ
11:16 09.07.2025 (የተሻሻለ: 11:24 09.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ብሪክስ ትራምፕ ችላ ሊሉት የማይችሉት የሀገራት ስብስብ እንደሆነ ባለሙያው ተናገሩ
“ብሪክስ የመጪው ጌዜ ታላቅ ስብስብ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የብሪክስ ሀገራት የ10% ቀረጥ ይጣልባቸዋል ማለታቸው ለዚህ ማሳያ ነው” ሲሉ በህንድ ኦብዘርቨር ሪሰርች ፋውንዴሽን ባልደረባ የሆኑት ሳሚር ባታቻሪያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ብሪክስ ለምዕራባውያን ኢኮኖሚያዊ የበላይነት የተሰጠ ምላሽ ብቻ ሳይሆን፤ የፆታ እኩልነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ሽብርተኝነትን በመዋጋት እና ዓለም አቀፍ የልማት ባንኮችን በመቅረጽ ላይ ያለ ባለብዙ ኃይል ነው ሲሉ አስረድተዋል።
የአፍሪካ ሀገራት ብሪክስን ለመቀላቀል ተሰልፈው የሚገኙ በመሆናቸው የቡድኑን እያደገ የመጣ ተፅዕኖ መካድ አይቻልም።
የትራምፕ ቀረጦች ብሪክስ ምን ያህል የማይገታ ቡድን እንደሆነ ያረጋግጣሉ ብለዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X