“ሞስኮን እደበድባለሁ” ሲሉ ትራምፕ ፑቲንን እንዳስፈራሩ የገለፁበትን ድምፅ እንዳገኘ ሲኤንኤን አስታወቀ
10:47 09.07.2025 (የተሻሻለ: 10:54 09.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
“ሞስኮን እደበድባለሁ” ሲሉ ትራምፕ ፑቲንን እንዳስፈራሩ የገለፁበትን ድምፅ እንዳገኘ ሲኤንኤን አስታወቀ
እንደ ሚዲያው ዘገባ ዶናልድ ትራምፕ ለለጋሾች ባደረጉት ንግግር ለቭላድሚር ፑቲን እና ለሺ ጂንፒንግ፤ ዩክሬን እና ታይዋን ላይ ወረራ የሚፈፅሙ ከሆነ ሞስኮ እና ቢጂንግን በቦምብ እደበድባለሁ ብለው እንዳስፈራሩ የገለፁበትን ልዩ የድምጽ ፋይል አግኝቷል።
“ዩክሬን ውስጥ ከገባህ ሞስኮን እደበድባለሁ፤ ምርጫ የለኝም እያልኩህ ነው” ሲሉ ትራምፕ ለፑቲን እንደተናገሩ ተዘግቧል፤ የቻይናው ፕሬዝዳንትም ቤጂንግን በተመለከተ ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው አክለዋል።
መሪዎቹ ማስፈራሪያውን በጥርጣሪ እንደተመለከቱት የገለፁት ትራምፕ፤ “10 በመቶ አምነውኛል” ሲሉ አፅዕኖት በመስጠት፤ ይህም ለእርሳቸው በቂ እንደነበር ተናግረዋል።
ቅጂው ትክክለኛ ከሆነ ትራምፕ ከፍተኛ ወታደራዊ ውጥረትን እንደ ድርድር መሣሪያ መጠቀም የዲፕሎማሲያዊ ስልታቸው እንዳደረጉ ያሳያል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የዩክሬን ግጭትን በ24 ሰዓታት ውስጥ እንደሚያስቆሙ በተደጋጋሚ ቃል ቢገቡም አካሄዳቸው ፅንፍ ወታደራዊ ማስፈራሪያዎች ላይ የተመሠረተ መስሏል።
የስምምነት ጥበብ — ወይስ አላስፈላጊ ድራማ?
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X