ብሪክስ ለትብብር እና ተጨባጭ እርምጃ ጊዜው አሁን እንደሆነ "ትክክለኛ መልዕክት" አስተላልፏል ሲሉ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር አስታወቁ

ሰብስክራይብ

ብሪክስ ለትብብር እና ተጨባጭ እርምጃ ጊዜው አሁን እንደሆነ "ትክክለኛ መልዕክት" አስተላልፏል ሲሉ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር አስታወቁ

አምባሳደር ልኡልሰገድ ታደሰ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ካደረጉት ቃለ-ምልልስ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 መሪዎች ለውጤታማ የዓለም አቀፍ ትብብር ቁርጠኛ እንደሆኑ አረጋግጠዋል፡- “ብሪክስ መፍትሄ ተኮር እንዲሁም የጋራ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል የተሻሻለ አጋርነት ነው።"

🟠 ዓለም አቀፍ ስርዓቶችን ለማሻሻል ጠንካራ ጥሪ ተላልፏል፦

የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ሊሻሻል ይገባል፤ “አፍሪካ በትንሹ ሁለት ቋሚ መቀመጫዎችን ማግኘት ይገባታል።"

አሁን ያለው የፋይናንስ መዋቅር “የታዳጊ ሀገሮችን ተገቢ የኢኮኖሚ ፍላጎቶች አያንፀባርቅም።”

🟠 ለአየር ንብረት ለውጥ እርምጃ እና ለአሳታፊ የዲጂታል ስርዓት ተሳትፎ ቃል ገብቷል፦

የአየር ንብረት ለውጥን መዋጋት፤

የ2030 የዘላቂ ልማት አጀንዳን ለማሳካት የዲጂታል ክፍተቶችን ማጥበብ።

🟠 የታዳጊ ሀገራትን ጥቅም የሚያስከብር ሁሉን አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት አስተዳደር እንዲኖር ግፊት ተደርጓል።

🟠 የጤና ደህንነት ቅድሚያ ተሰጥቶታል፡- “የሁሉም ሰው ደህንነት እሰኪጠበቅ ድረስ የማንም ሰው ደህንነት እርግጥ አይደለም።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0