ቱሪዝም ሚኒስቴር ቪዚት ኢትዮጵያ የተሰኘ ዲጅታል መድረክ ይፋ አደረገ
18:15 08.07.2025 (የተሻሻለ: 19:34 08.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቱሪዝም ሚኒስቴር ቪዚት ኢትዮጵያ የተሰኘ ዲጅታል መድረክ ይፋ አደረገ
ቴክኖሎጂውን ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በትብብር እንዳለማው የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ አስታውቋል፡፡
ቪዚት ኢትዮጵያ ፈርጀ-ብዙ ጠቀሜታዎችን የሚያስገኝ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ውጤት ሲሆን፦
የቱሪዝም ፀጋዎችን፣ የቱሪስት መዳረሻዎችን፣ የቱሪዝም ምርትና አገልግሎቶችን እንዲሁም የኢትዮጵያን ልዩ የቱሪዝም መገለጫዎች በአንድ ኦንላይን ሥፍራ ለማስተዋወቅ ያስችላል፣
በቱሪዝም እሴት ሰንሰለት ውስጥ የተሠማሩ ቁልፍ የቱሪዝም ተዋንያንን በአንድ ሥፍራ ያገናኛል፣
ጎብኝዎች የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስህቦች፣ አገልግሎቶች፣ ምርቶች እና የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች የተመለከቱ ትክክለኛ እና ፈጣን መረጃዎችን እንዲገኙ ያስችላል፣
ሕጋዊ የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ከሕገ-ወጦች ለመለየት እና ግልፅና ፍትሐዊ የቱሪዝም ንግድ ለማስፈን ያስችላል፡፡
በአጠቃላይ መድረኩ የኢትዮጵያ ቱሪዝም የዲጅታል ሱቅ/መገበያያ መስኮት ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል ተዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X