በኬንያ "የሳባ ሳባ" ተቃውሞዎች በትንሹ 11 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውን ፖሊስ አስታወቀ

ሰብስክራይብ

በኬንያ "የሳባ ሳባ" ተቃውሞዎች በትንሹ 11 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውን ፖሊስ አስታወቀ

የብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት በሰጠው መግለጫ አብዛኞቹ ኬንያውያን ሕግና ሥርዓት ቢያከብሩም አንዳንድ ሰዎች በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተሰማርተው እንደነበር ገልጿል።

ፖሊስ የሚከተሉትን ክስተቶች ሪፖርት አድርጓል፦

◾ የመቁስል አደጋ ፦ 52 ፖሊሶች፣ 11 ሲቪሎች፣

◾ የወደሙ ተሽከርካሪዎች፦ 12 የፖሊስ፣ 4 የሲቪል፣ 3 የመንግሥት፣

◾ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር፦ 567 (አንድ የፓርላማ አባልን ጨምሮ)።

በተመሳሳይ የኬንያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ትናትና በተካሄዱት ተቃውሞዎች ላይ የነበሩትን አሳሳቢ ስጋቶች እንደሚከተለው አስታውቋል።

◻ ከመጠን ያለፈ የመንገድ መዘጋት፦ በፖሊስ እገዳዎች ምክንያት እንቅስቃሴዎች በከፍተኛ ደረጃ መስተጓጎል የደረሰባቸው ሲሆን ይህም በዜጎች የመሥራት አቅም ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።

◻ የንግድ ተቋማት መዘጋት፦ ዘረፋ (በስድስት ክልሎች ሪፖርት ተደርጓል) በሚል ስጋት የተነሳ የንግድ ተቋማት በብዛት ተዘግተዋል።

◻ ሕገ-ወጥ የፖሊስ ተግባር፦ ፖሊስ በአደባባይ በሚደረጉ ሰልፎች ወቅት ዩኒፎርም ያልለበሱ እና ማንነታቸው የማይለይ መኮንኖች እንዲገኙ ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ያስተላለፈውን ትዕዛዝ አላከበረም።

◻ የወንበዴዎች ስብስብ፦ በናይሮቢ እና ኤልዶሬት ከፖሊስ ጎን ለጎን ስለታማ መሳሪያዎችን፣ ድንጋዮችን እና ቤት ውስጥ የሚሠሩ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ወንበዴዎች ሪፖርት ተደርጓል።

አክሎም ባለፈው ሳምንት ከ20 በላይ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተደበድበው፣ ታስረው፣ ክስ ተመስርቶባቸው ወይም ተጠርተው እንደነበር ፤ በተጨማሪ መንግሥት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን "ማንገላታቱን" እና ሕጋዊ የሰብዓዊ መብት ሥራዎችን ወንጀል አድርጎ መቁጠሩን ወዲያውኑ ማቆም አለበት ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።

በመካሄድ ላይ ያሉት የሳባ ሳባ" ተቃውሞዎች የአንድ ፓርቲ አገዛዝን በመቃወም እ.ኤ.አ በ1990 የተደረጉትን ሰልፎች በማስታወሰ በኑሮ ውድነት፣ በሙስና እና በፖሊስ ጭካኔ ላይ ትኩረታቸውን እንዳደረጉ ተዘግቧል፡፡

ከማህበራዊ የትስስር ገፆች የተገኙ ምሥሎች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በኬንያ የሳባ ሳባ ተቃውሞዎች በትንሹ 11 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውን ፖሊስ አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በኬንያ የሳባ ሳባ ተቃውሞዎች በትንሹ 11 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውን ፖሊስ አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0