የአሜሪካ ኤምባሲ ለናይጄሪያ የተማሪ ቪዛ አመልካቾች የማህበራዊ ትሥሥር ገፅ ፍተሻ እንደሚያካሂድ አስታወቀ
16:53 08.07.2025 (የተሻሻለ: 16:54 08.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአሜሪካ ኤምባሲ ለናይጄሪያ የተማሪ ቪዛ አመልካቾች የማህበራዊ ትሥሥር ገፅ ፍተሻ እንደሚያካሂድ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ኤምባሲ ለናይጄሪያ የተማሪ ቪዛ አመልካቾች የማህበራዊ ትሥሥር ገፅ ፍተሻ እንደሚያካሂድ አስታወቀ
ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ ለ "ኤፍ"፣ "ኤም"፣ "ጄ" የተማሪና የልውውጥ ቪዛ ለማግኘት የሚያመለክቱ ናይጄሪያውያን የማህበራዊ ትሥሥር ገጾቻቸውን "ይፋ" ማድረግ እንዳለባቸው አስታውቋል።
ይህ ፖሊሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የተደረገው በሰኔ ወር ሲሆን ወዲያውኑ ተግባራዊ ሆኗል። እንደ ስቴት ዲፓርትመንት ገለጻ ሂደቱ የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ጥብቅ የቪዛ ማጣሪያ አካል ነው።
የናይጄሪያ ባለሥልጣናት በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጡም።
በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እ.ኤ.አ ከ2023-2024 ከ20 ሺህ በላይ የናይጄሪያ ተማሪዎች በአሜሪካ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች መቀላቀላቸውን ገልጿል። በዚህም ናይጄሪያ በአሜሪካ ውስጥ ካሉ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች በቁጥር 7ኛ ደረጃን አግኝታለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X