ብሪክስ ለትራምፕ የቀረጥ ማስፈራሪያ "እኛ ገዥ አንፈልግም" ሲል ምላሽ ሰጠ

ብሪክስ ለትራምፕ የቀረጥ ማስፈራሪያ "እኛ ገዥ አንፈልግም" ሲል ምላሽ ሰጠ
የብሪክስ አባል ሀገራት ትራምፕ ከብሎኩ ጋር በሚሰለፉ ሀገራት ላይ 10 በመቶ ቀረጥ እንደሚጥሉ የሰጡትን ማስጠንቀቂያ ውድቅ አድርገዋል። በምላሹም "ፀረ-አሜሪካዊ" መባላቸውን አስተባብለው ለህብረ-ብሔራዊነተ፣ ለትብብር እና ለዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አስተዳደር ማሻሻያ ቁርጠኛ እንደሆኑ አፅንኦት ሰጥተዋል።
የብሪክስ መሪዎች የሰጡት ምላሽ፦
የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ፦
"አሜሪካን የሚያክል ሀገር የሚመራ ፕሬዝዳንት ዓለምን በግልፅ ማስፈራራቱ አግባብ የለውም።” በተጨማሪም ብሪክስ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ትብብር አማራጭ ማዕቀፎችን ለመገንባት እንጂ ከአሜሪካ ጋር በተቃርኖ የመቆም ፍላጎት እንደሌለው ለጋዜጠኞች በሰጡት ምላሽ አፅንኦት ሰጥተዋል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ፦
"የንግድ እና የቀረጥ ጦርነት አሸናፊ የላቸውም፤ በተጨማሪም የክልከላ ፖሊሲ የትም አያደርስም። […] ብሪክስ እያደጉ በሚገኙ እና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት መካከል ትብብር ለመፍጠር ጠቃሚ መድረክ ነው። ግልጽነትን፣ አካታችነትን እና የሀገራትን የጋራ ጥቅም መሠረት የሚያደርግ ትብብርን ያበረታታል። ለግጭት የተመሠረተ ቡድን አይደለም። እንዲሁም ማንኛውንም ሀገር ዒላማ አያደርግም፡፡"
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፦
"በብሪክስ ውስጥ ያለው ትብብር በጭራሽ በማንኛውም የሶስተኛ ወገን ሀገር ላይ ያነጣጠረ አልነበረም፤ ወደፊትም አይሆንም። […] በእያንዳንዱ አባል ሀገር ፍላጎት ላይ በመመሥረት ተመሳሳይ አካሄድን የሚጋሩ እና ትብብር እንዴት እንደሚከውን የማሳየት የጋራ ራዕይ ያላቸው ሀገራት ስብስብ ነው።"
የደቡብ አፍሪካ የንግድ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ካሚል አሊ፦
"እኛ ፀረ-አሜሪካዊ አይደለንም። […] ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በተያያዘ የንግድ ስምምነታችንን አክብራ መደበኛ ግንኙነት እስክትጀምር እየጠበቅን ነው፤ ይሁን እንጂ ውይይታችን ገንቢ እና ፍሬያማ ሆኖ ቀጥሏል" ሲሉ ለብሪታኒያ የመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
ሌሎች አባላት እና አጋሮች፦
ህንድ ወዲያውኑ ይፋዊ ምላሽ ባትሰጥም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከሌሎች የብሪክስ መሪዎች ጋር በመሆን "ንግድን የሚያዛቡ እና ከዓለም ንግድ ድርጅት ሕጎች ጋር የማይጣጣሙ የአንድ ወገን ቀረጥ እና ቀረጥ ነክ ያልሆኑ እርምጃዎች መጨመርን" የሚያስጠነቅቅ የጋራ መግለጫ ፈርመዋል።
ናይጄሪያ ከብሪክስ መርሆዎች ጋር እንደምትሰለፍ በድጋሚ ታረጋግጣላች ሲሉ በብሪክስ ስብሰባ ላይ የተናገሩት ፕሬዝዳንት ቲኑቡ፤ አቡጃ "ለሁሉም ዘላቂና አካታች ልማት ለሚያመጣ ስትራቴጂካዊ ትብብር" ቁርጠኛ እንደሆነች አክለዋል።
የትራምፕ ዛቻ ብሪክስ በብራዚል ያካሄደው ጉባኤ መጠናቀቁን ተከትሎ የመጣ ሲሆን መሪዎቹ ዓለም አቀፍ ተቋማት ማሻሻያዎች እንዲያደረጉ ጥሪ አቅርበው የአንድ ወገን የንግድ እርምጃዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ተችተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X