ፖሊስ በአርሜኒያ በእስር ላይ የሚገኙት የነጋዴው ካራፔትያንን የኃይል ድርጅት ወረረ
14:14 08.07.2025 (የተሻሻለ: 14:44 08.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፖሊስ በአርሜኒያ በእስር ላይ የሚገኙት የነጋዴው ካራፔትያንን የኃይል ድርጅት ወረረ
በሩሲያ-አርሜኒያዊው ነጋዴ ሳምቬል ካራፔትያን ባለቤትነት ሥር የሚገኘው የአርሜኒያ ኤሌክትሪክ ኔትወርክ የቢሮ ሕንፃ ውስጥ ሠራተኞች እንዳይገቡ መከልከላቸውን የኩባንያው ቃል አቀባይ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ወረራው ካራፔትያን ከወንጀል ጋር በተያያዘ አስቸኳይ ምርመራ ከተከፈተባቸው በኋላ የመጣ ነው ሲሉ የአርሜኒያ የምርመራ ኮሚቴ ቃል አቀባይ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ℹ ካራፔትያን ከመንግሥት ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችውን የአርሜኒያ ሐዋርያዊት ቤተ- ክርስቲያንን በግልጽ ይደግፉ የነበረ ሲሆን ሥልጣን ለመያዝ በማነሳሳት ወንጀል ተከሰው ለሁለት ወር ያህል በእስር እንዲቆዩ ተወስኖባቸዋል፡፡ እርሳቸው ግን ክሱን አስተባብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/