የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት አምስት ሚሊየን ሀገር በቀል ችግኞችን ለሰባተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት አምስት ሚሊየን ሀገር በቀል ችግኞችን ለሰባተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት አምስት ሚሊየን ሀገር በቀል ችግኞችን ለሰባተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.07.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት አምስት ሚሊየን ሀገር በቀል ችግኞችን ለሰባተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ 

ተቋሙ የዘንድሮውን ሳይጨምር መርሃ-ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ16 ሚሊየን በላይ ሀገራዊ ችግኞችን መትከሉን ገልጿል።

የሀገር በቀል እፅዋት ሥነ-ምህዳራዊ እና መድኃኒታዊ ጠቀሜታ ላይ አፅንኦት የሰጡት የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪ አበራ ስዩም "አንዴ ከተተከሉ በኋላ እነዚህ ዝርያዎች አነስተኛ እንክብካቤ የሚጠይቁ እና በተፈጥሯቸው ድርቅንና በሽታን የመቋቋም አቅም ያላቸው ናቸው" ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዝርያዎች ወይራ፣ ዋንዛ፣ ኮሶ፣ የሀበሻ ፅድ እና ጥቁር እንጨት እንደሆኑ የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0