"ኢትዮጵያ ከብሪክስ ጋር ባላት አጋርነት ፍሬያማ እየሆነች ነው" - የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"ኢትዮጵያ ከብሪክስ ጋር ባላት አጋርነት ፍሬያማ እየሆነች ነው" - የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
ኢትዮጵያ ከብሪክስ ጋር ባላት አጋርነት ፍሬያማ እየሆነች ነው - የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.07.2025
ሰብስክራይብ

"ኢትዮጵያ ከብሪክስ ጋር ባላት አጋርነት ፍሬያማ እየሆነች ነው" - የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ በሪዮ ዴ ጂኔሮ በተካሄደው 17ተኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያ የነበራትን ተሳትፎ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው የተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች፦

በጉባኤው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እና ጣልቃ አለመግባት መርህን በማጉላት አቋሟን ገልፃለች።

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ድምጽ በሁሉም ዓለም አቀፍ ተቋማት በእኩልነት መወከል እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተዋል።

ዐቢይ በኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ዘርፎች ኢትዮጵያ ከብሪክስ ጋር ካላት አጋርነት ተጠቃሚ እንደሆነች ገልፀዋል።

ብሪክስ የልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ እንደሚሆን አንስተዋል።

 ኢትዮጵያ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች መሆኑን እና በዚህ ዘርፍ ከብሪክስ ሀገራት ጋር ለመተባበር እንደምትፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አበክረው ተናግረዋል።

 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ሀገሪቱ ዓለም እንዲከተላት የሚያስችል ተግባራዊ ምሳሌ እያሳየች መሆኑን ገልፀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0