የብሪክስ አዲሱ የልማት ባንክ ለአባል ሀገራቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት በብሪክስ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ሸርፓ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

የብሪክስ አዲሱ የልማት ባንክ ለአባል ሀገራቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት በብሪክስ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ሸርፓ ተናገሩ

ቤን ጁበርት ባንኩ ከብሪክስ የላቁ ተቋማዊ ስኬቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን በማንሳት አገልግሎቱን ይበልጥ ለማስፋት እየተሠራ መሆኑን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል

"አዲሱ የልማት ባንክ ይበልጥ መስፋት እንዳለበት እናምናለን። ባንኩ እየሰፋ የመምጣቱን እውነታም ዕውቅና መስጠት ተገቢ ነው። እንደ እውነቱ ባንኩ ከብሪክስ አባል ሀገራት ቁጥር አስቀድሞ ነው መስፋት የጀመረው። እ.አ.አ በ2022 ግብጽ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ባንግላዲሽ እና ኡራጋይ ባንኩን መቀላቀላቸውን አይተናል። በቅርቡም አልጄሪያ ባንኩን መቀላቀሏን ተመልክተናል" ብለዋል።

እ.አ.አ በ2014 የተቋቋመው አዲሱ የልማት ባንክ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚሠሩ ፕሮጀክቶችን የመደገፍ በግልጽ የተቀመጡ ኃላፊነቶች እንዳሉበትም አመላክተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0