ፔንታጎን የመከላከያ መሳሪያዎችን በቅርቡ ወደ ዩክሬን እንደሚልክ አስታወቀ
10:46 08.07.2025 (የተሻሻለ: 10:54 08.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፔንታጎን የመከላከያ መሳሪያዎችን በቅርቡ ወደ ዩክሬን እንደሚልክ አስታወቀ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ለዩክሬን ተጨማሪ መሳሪያዎችን እንደሚልኩ ቃል ገብተው የነበረ ሲሆን ይህም በዋነኛነት "የመከላከያ" መሳሪያዎችን እንደሚመለከት አጽንኦት ሰጥተዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ የያዘ ማንኛውም ጭነት የሩሲያ ሕጋዊ ኢላማ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ በማቅረብ "በእሳት እየተጫወቱ ነው" ሲሉ አስረግጠዋል። ክሬምሊን ዩክሬንን በምዕራባውያን የጦር መሳሪያዎች ማጨናነቅ በሩሲያ-ዩክሬን ድርድር ስኬት ላይ አስተዋፅኦ እንደማያደርግ እና አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው በአበክሮ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X