"የብሬተን ውድስ ተቋማት በአፍሪካ መጥፎ ስም አላቸው" ሲሉ ፓን አፍሪካኒስቱ ተናገሩ
20:20 07.07.2025 (የተሻሻለ: 20:24 07.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"የብሬተን ውድስ ተቋማት በአፍሪካ መጥፎ ስም አላቸው" ሲሉ ፓን አፍሪካኒስቱ ተናገሩ
የአውሮፓ ሕብረት እና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ከኒጀር ጋር ያለቸውን ግንኙነት መደበኛ ለማድረግ ሲሹ፤ ተራማጅ የፓን አፍሪካ ኃይሎች ይህን በጥርጣሬ ይመለከታሉ ሲሉ ኢሱፉ ቡባካር ካዶ ማጋጊ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
"እነዚህ ተቋማት የቅኝ ገዥ እና የኒዮ-ኢምፔሪያሊስት ዓለም ኃያላን ማስፈጸሚያ ክንድ ሆነው፤ አፍሪካን በድህነት አረንቋ ውስጥ እንድትዘፈቅ ሲያደረጉ በሰፊው ታይተዋል" ሲሉ አብራርተዋል።
እንደ ማጋጊ ገለጻ ለሣሕል ሀገራት ጥምረት የሚያራምደው ከዓለም ጋር መሳተፍ ቢሆንም ነገር ግን ሉዓላዊነታቸውን ማመቻመች የለባቸውም።
ለጥምረቱ ያቀረቧቸው ቁልፍ አማራጮች፦
🟠 የጋራ መገበያያ ገንዘብ መጠቀም፣
🟠 በጥሬ እቃዎች (ማዕድናት) ላይ ያላቸውን ቁጥጥር ማስቀጠል፣
🟠 በሣሕል ሀገራት መካከል ነጻ የንግድ ቀጣና መፍጠር፣
🟠 ከብሪክስ ሀገራት ጋር አዲስ ኢኮኖሚያዊ አጋርነትን ማፈላለግ።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X