ብሪክስ በአባል ሀገራቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ የፍላጎት አና አቅርቦት ልዩነት ለማጣጣም አይነተኛ የመገናኛ ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን ተናገሩ

ሰብስክራይብ

ብሪክስ በአባል ሀገራቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ የፍላጎት አና አቅርቦት ልዩነት ለማጣጣም አይነተኛ የመገናኛ ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን ተናገሩ

አፍሪካ ሰፊ አምራች ኃይል ያላት አሕጉር መሆኗን ያወሱት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፤ በዚህ ረገድ ብሪክስ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ እና በዕውቀት ሽግግር አብሮ መሥራት የሚያስችል ምቹ መደላድል መፍጠሩን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ኢኖቬሽን እና ሥራ ፈጣሪነት የኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ልብ እና ማዕከል ናቸው። አንደ አህጉር ያለንን ይህን እምቅ አቅም ለማሳደግም ከሀገራት እና እንደ ብሪክስ ካሉ ጥምረቶች ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነን" ሲሉ ከ3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ጎን ለጎን አስተያየታቸውን ሰጥተውናል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0