የጤና መድህን ከ63 ሚሊየን በላይ ለሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ተደራሽ ሆነ ተባለ
19:50 07.07.2025 (የተሻሻለ: 19:54 07.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የጤና መድህን ከ63 ሚሊየን በላይ ለሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ተደራሽ ሆነ ተባለ
በ2017 የበጀት ዓመት ዜጎች ከማኅበራዊ የጤና መድህን ተጠቃሚ መሆናቸውን የጤና ሚኒስትሯ መቅደስ ዳባ አስታውቀዋል።
በአዲስ አበባ የዓመቱን አፈጻጸም ባቀረቡበት ንግግራቸው ቁልፍ ስኬቶችን ጠቅሰዋል፡፡
"ጤናማ እና አምራች ትውልድ ለመገንባት ሥራዓተ ምግብን ማሻሻል አስፈላጊ ነው።"
በ10 ዓመቱ የምግብና የሥርዓተ-ምግብ ስትራቴጂ እና በቀጠለው የሰቆጣ ቃል ኪዳን በ2017 ወደ 334 ወረዳዎች መድረሱን እና በ2018 ወደ 520 ወረዳዎች በማዳረስ በ2022 ዓ.ም የምግብ እጥረትን ለማስወገድ መተለሙን ጠቁመዋል።
እንደ አረንጓዴ አሻራ ያሉ ሀገራዊ ንቅናቄዎች የኢትዮጵያን የሥርዓተ-ምግብ ለማጠናከር ወሳኝ መሆናቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሯ፤ በአሁኑ ወቅት የጤና አገልግሎት ሽፋን ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን በሪፖርታችው አቅርበዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
