ደቡብ አፍሪካ ለአሜሪካ ባላንጣ አይደለችም - የሀገሪቱ ንግድ ሚኒስቴር
19:35 07.07.2025 (የተሻሻለ: 19:44 07.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ ለአሜሪካ ባላንጣ አይደለችም - የሀገሪቱ ንግድ ሚኒስቴር
"የንግድ ስምምነታችንን በተመለከተ አሁንም ከአሜሪካ ይፋዊ ምላሽ እንጠብቃለን፤ ነገር ግን ውይይታችን ገንቢ እና ፍሬያማ ነው። ቀደም ሲል እንደተናገርነው ፀረ-አሜሪካዊ አይደለንም" ሲሉ የንግድ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ካሚል አሊ ለምዕራብ የዜና ወኪል ተናግረዋል።
ℹ ትራምፕ የብሪክስን ፖሊሲዎችን በሚደግፉ ሀገራት ላይ ተጨማሪ የ10 በመቶ ቀረጥ እጥላለሁ በማለት ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ የሰጡት አስተያየት ነው፡፡
ከ2011 ጀምሮ የብሪክስ አባል የሆነችው ደቡብ አፍሪካ፤ ግንቦት 13 ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ከትራምፕ ጋር በተወያዩ ጊዜ የንግድ ስምምነት ሰነድ አቅርባ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ረቂቅ ስምምነቱ ብዙ ጊዜ የተጣራ ቢሆንም ምንም አይነት ቀጣይ ውይይቶች አልተደረጉም፡፡
ትራምፕ በሚያዚያ ወር በደቡብ አፍሪካ ምርቶች ላይ የጣሏቸው ልዩ ቀረጦች፦
30% በወይን፣
25% በብረት እና በብረት ውጤቶች፣
25% በመኪናዎች እና መለዋወጫዎች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X