"የብሪክስ አባል ሀገራት በራሳቸው ገንዘብ የመገበያየት እሳቤ ዶላርን በማዳከም አውድ ሊታይ አይገባም"

ሰብስክራይብ

"የብሪክስ አባል ሀገራት በራሳቸው ገንዘብ የመገበያየት እሳቤ ዶላርን በማዳከም አውድ ሊታይ አይገባም"

"እኛ በራሳችን ገንዘቦች መገበያየት የምንፈልገው መገበያያዎቻችን በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ተሰራጭተው እንደሚገኙ ስለምናምን ነው። ይህም ገንዘብ ለመቆጠብ ያስችለናል" ሲሉ በብሪክስ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ሸርፓ ቤን ጁበርት ከስፑትኑክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

ቤን ጁበርት የአፍሪካ ሀገራት ግብይታቸውን በራሳቸው ገንዘብ ማድረግ ቢችሉ አሕጉሪቱ በዓመት ከግብይት ጋር የተያያዙ ከ5 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪዎችን ማዳን እንደምትችል የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ጥናትን ዋቢ አድርገው አስረድተዋል።

ይህም ገንዘብ በማደግ ላይ ለምትገኘው አፍሪካ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ማኀበራዊ ጥይቄዎችን ለመመለስ እንደሚያግዝ አጽዕኖት ሰጥተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0