የብሪክስ አባል ሀገራት ቁጥር ማደግ የጥምረቱን ራዕይ ይበልጥ እንደሚያልቀው የብሪክስ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ሸርፓ ቤን ጁበርት ተናገሩ

ሰብስክራይብ

የብሪክስ አባል ሀገራት ቁጥር ማደግ የጥምረቱን ራዕይ ይበልጥ እንደሚያልቀው የብሪክስ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ሸርፓ ቤን ጁበርት ተናገሩ

የጥምረቱ አባል ሀገራት ቁጥር ከ5 ወደ 10 ማደጉ የተጠናከረ ወዳጅነት እና ሰፊ አቅም ለመፍጠር እንደሚያግዝም ምክትል ሸርፓው በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ እየተካሄደ የሚገኘውን የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ አስመልክቶ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስታውቀዋል።

"እኛ አሁን ይበልጥ ጊዜ ወስዶ ወዳጅነትን በማጠናከር ምዕራፍ ላይ እንዳለን አስባለሁ። በዚህ ምዕራፍ የሚሆነው ሌላኛው ነገር የተወሰኑ የፍላጎት መጠኖችን መስዕዋት ማድረግ ነው። በዚህ መንገድ የሚፈጠረው መቀናጀትም የሚበልጡ ራዕዮችን ይወልዳል" ብለዋል።

ምክትል ሸርፓው ብሪክስ ለአባል ሀገራቱ ምቹ የፖሊሲ መድረክ እንዲሁም በመደጋገፍ አብሮ ማደግ የሚያስችል አውድ መፍጠሩንም አመላክተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0