- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ዲግሪ ወይስ ጥበብ? “የተማረ”፦ ሊጤን የሚገባው ሃሳብ

ዲግሪ ወይስ ጥበብ? “የተማረ”፦ ሊጤን የሚገባው ሃሳብ
ሰብስክራይብ
ዛሬ ሰኔ 30 ነው! ሰኔ 30 በተለምዶ የየዓመቱ የትምህርት ጊዜ መዝጊያ ተደርጎ ይወሰዳል።
ይህንኑ ዕለት መነሻ ያደረገዉ የዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ላይ በጊዜ ሂደት የታዩ ለውጦችን - ንድፈ-ሃሳብ ላይ ብቻ ወይም 'ሽምደዳ' ላይ ከማተኮር ይልቅ ተማሪዎች በነጻነት ምክንያታዊ አስተሳሰብን እንዲያጎለብቱ ወደሚያስችል የመማር ማስተማር ሂደት መቀየርን እንዳስሳለን።
ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያ ከሆኑት ከአቶ ማሞ መንገሻ ጋር በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ስለታዩ ለውጦች እና አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው የብቁ መምህራን እጥረት ዙሪያ ውይይት እናደርጋለን፡፡
አቶ ማሞ አንድን ሰው “የተማረ” ሊያስብለው ስለሚችለው ሁኔታ ሲያብራሩ:-
“አንድ ሰው ተማረ የሚባለው የሰማውን እንዳለ የማይቀበል፣ እወነት ነው አይደለም ብሎ ችግር ሲገጥመው ዝም ብሎ ሰዎችን ጠይቆ ብቻ ሳይሆን ራሱ ችግርን የሚፈታ […] ምርምር ሊሰራ የሚችል፤ የዚህ ዐይነት ሰው ነው”፡፡
አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው የብቁ መምህራን እጥረት ዙሪያ:-
“በአሁኑ ሰዓት በዩኒቨርስቲ ደረጃ የሚገቡት ተማሪዎች ጥቂት ናቸው፡፡ ከእነሱም ውስጥ አንድም ወደ መምህርነት የመጣ ስለሌለ ወደፊት የመምህራን እጥት ሊያጋጥም እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ” — በማለት አቶ ማሞ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡
እኛም በዚህ ራይዚንግ ሳውዝ በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ላይ ያደረግነውን ዳሰሳ እንድትከታተሉ ጋበዝን!
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify
አዳዲስ ዜናዎች
0