በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተጣብቀው የተወለዱ ሕጻናትን የመለየት ቀዶ ሕክምና በስኬት ተጠናቀቀ
17:51 07.07.2025 (የተሻሻለ: 17:54 07.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተጣብቀው የተወለዱ ሕጻናትን የመለየት ቀዶ ሕክምና በስኬት ተጠናቀቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተጣብቀው የተወለዱ ሕጻናትን የመለየት ቀዶ ሕክምና በስኬት ተጠናቀቀ
ቀዶ ሕክምናው 3 ሠዓት ተኩል ፈጅቷል፡፡ ተጣብቀው ከተወለዱት 1ኛው ጥገኛ ሲሆን ዋናው ሕጻን ልጅ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ነው የታወቀው፡፡ መንትዮቹ ሆድ አከባቢ የሚገናኙ ሲሆን፤ ጉበት ይጋሩ እንደነበር ሐኪሞች ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል፡፡
ጥገኛ መንትያው ያልጎለበተ ቢሆንም የራሱ የሆነ የሆድ እቃ፣ ሳንባ፣ ኩላሊት፣ አነስተኛ ልብ እና ጭንቅላት የመሳሰሉ የሰውነት ክፍሎች እንደነበሩትም ጠቅሰዋል።
ቀዶ ሕክምና የተደረገለት የ6 ወር ዕድሜ ያለው ሕጻን ነው ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X