የብሪክስ ስብሰባ በብራዚል፦ ተሳታፊዎችና አጀንዳዎች

የብሪክስ ስብሰባ በብራዚል፦ ተሳታፊዎችና አጀንዳዎች
በሪዮ ዴጄኔሮ በብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የሚመራው 17ኛው የብርክስ ጉባኤ፤ የሁሉም የብሪክስ አባል ሀገራት እና የዘጠኝ አጋር ሀገራት ተወካዮች ይስተናገዱበታል። ከዋና ተሳታፊዎች ውስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፦
ሕንድ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣
ደቡብ አፍሪካ፡ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣
ግብጽ፡ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታሕ ኤል-ሲሲ፣
ኢትዮጵያ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣
ኢራን፡ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን፣
ኢንዶኔዥያ፡ ፕሬዝዳንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ፣
የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች፡ ፕሬዝዳንት መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው አቻቸው ዢ ጂንፒንግ በአካል አይገኙም።
ናይጄሪያ እና ኡጋንዳን ጨምሮ ሁለት የአፍሪካ አጋር ሀገራት ይገኛሉ።
ጉባኤው በሦስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ ያተኩራል፡-
🟠 የዓለም አቀፍ አስተዳደር ሥርዓትን ማሻሻል
ብሪክስ እንደ የተመድ፣ የዓለም ንግድ ድርጅት እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ያሉ ተቋማትን ለማሻሻል አልሟል፡፡
🟠 ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር
በብሪክስ ሀገራት መካከል ንግድን በማበረታታት እና አማራጭ የክፍያ ሥርዓቶችን በመዘርጋት ከምዕራባውያን ምንዛሬዎች ጥገኛነት መውጣት።
🟠 ዓለም አቀፍ ደህንነትን ማረጋገጥ
አጀንዳው የሳይበር ደህንነት፣ ዘላቂ ልማት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የመካከለኛው ምስራቅ ግጭትን ይዳስሳል፡፡
የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ በቦታው ይገኛል ላይ! አዳዲስ መረጃዎችን ይከታተሉ!
በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የመነጨ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X