የሆሊውድ "ዎክ ኦፍ ፌም" ኮከብ ያገኘች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ዘፋኝ

ሰብስክራይብ

የሆሊውድ "ዎክ ኦፍ ፌም" ኮከብ ያገኘች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ዘፋኝ

ቤኒናዊቷ አንጀሊክ ኪጆ በሆሊውድ የንግድ ምክር ቤት ተመረጠው በሎስ አንጀለስ ዝነኛው "ዎክ ኦፍ ፌም" ኮከብ ከሚቀበሉ 36 አርቲስቶች አንዷ ሆናለች።

ከሉፒታ ኒዮንግኦ፣ ቻርሊዝ ቴሮን እና ባሲል ራትቦን ከመሳሰሉ ትውልደ አፍሪካውያን አርቲስቶች በመቀጠል ታሪክ ሠርታለች።

የቤኒን ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎን “በአስገራሚ ጉዞዋና በዚህ ስኬቷ ለሁሉም ምሳሌ ትሆናለች” ሲሉ የአርቲስቷን “አስደናቂ ተሰጥኦ እና ታታሪነት” አድንቀዋል።

በረጅም የሥራ ዘመኗ ዘፋኟ አምስት የግራሚ ሽልማቶችን እና በ2023 የፖላር ሙዚቃ ሽልማትን አሸንፋለች። በአምስት ቋንቋዎች ማለትም የደቡብ ቤኒኑን ፎን፣ ፈረንሳይኛ፣ ዮሩባ፣ ሚና እና እንግሊዝኛ ትናገራለች።

የ64 ዓመቷ አንጀሊክ ኪጆ የዩኔስኮ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር እንዲሁም በአፍሪካ ያሉ ወጣት ሴቶችን የሚያስተምር እና የሚደግፍው የባቶንጋ ፋውንዴሽን መሥራች ናት፡፡

"ዎክ ኦፍ ፌም" ከዋክብት የሚደምቁበት ቀን ገና አልተገለጸም፤ ነገር ግን አንድ ነገር እርግጥ ነው፤ ይህም አንጀሊክ ኪጆ ሆሊውድን ማብራቷ ነው!

የሆሊዉድ "ዎክ ኦፍ ፌም" - በሆሊዉድ ኢለቫርድ እና ቫይን ጎዳና ከ2 ሺህ 700 በላይ በቴራዞ እና በነሐስ ኮከቦች ተንቆጥቁጦ የተዘረጋ ታሪካዊ የእገረኞች መንገድ ነው፡፡ የጥብብ ኢንዱስትሪ ሰዎች ላበረከቱት አስተዋፅኦ ክብር የሚሰጥበት ነው፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሆሊውድ "ዎክ ኦፍ ፌም" ኮከብ ያገኘች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ዘፋኝ
የሆሊውድ ዎክ ኦፍ ፌም ኮከብ ያገኘች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ዘፋኝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.07.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0