አፍሪካውያን በአህጉሪቱ ለሚመረቱ ክትባቶች “ቀዳሚ ሸማቾች መሆን አለባቸው” ሲሉ ቡርኪና ፋሷዊው ዶክተር ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካውያን በአህጉሪቱ ለሚመረቱ ክትባቶች “ቀዳሚ ሸማቾች መሆን አለባቸው” ሲሉ ቡርኪና ፋሷዊው ዶክተር ተናገሩ
አፍሪካውያን በአህጉሪቱ ለሚመረቱ ክትባቶች “ቀዳሚ ሸማቾች መሆን አለባቸው” ሲሉ ቡርኪና ፋሷዊው ዶክተር ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.07.2025
ሰብስክራይብ

አፍሪካውያን በአህጉሪቱ ለሚመረቱ ክትባቶች “ቀዳሚ ሸማቾች መሆን አለባቸው” ሲሉ ቡርኪና ፋሷዊው ዶክተር ተናገሩ

አፍሪካ በጤና ጥበቃ ረገድ ራሷን መቻል አለባት ሲሉ የእንስሳት፣ የማይክሮ ባዮሎጂ፣ ቫይሮሎጂ እና ኤፒዲሞሎጂ ዶክተር ዘኪባ ታርናጋዳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

የታርናጋዳ ተማጽኖ አፍሪካ በክትባት ምርት ራሷን በመቻል በኩል ተጨባጭ መሻሻል እያሳየች ባለችበት ወቅት የመጣ ነው። በ2024 በሴኔጋል የተመረቀው የዲያምኒያዲዮ ቫኪኖፖሌ የመድኃኒት ማምረቻ በአስደናቂ ምሳሌነት ተወስቷል። ይህ አዲስ ማምረቻ ከ5 እስከ 30 ሚሊየን የሚደርሱ በተለይም የቢጫ ወባ ክትባቶችን የማምረት አቅም አለው።

"ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሴኔጋልን ክትባት መሸመት አለባቸው። ይሁን እንጂ ውቅያኖሶችን አቋርጠው ከሌላ ቦታ ክትባቶችን መግዛት የሚመርጡ ሀገራት እንዳሉ አስተውያለሁ። በአፍሪካ የሚመረተውን መግዛት አይፈልጉም" ብለዋል ተመራማሪው።

የአፍሪካ ምርት ጠል አዝማሚያዎች እንድሚያሰጋቸውና እናዳጅ ሆኖ እንዳገኙትም ተናግረዋል።

የውጭ ገንዘብ ድጋፍ በተለይም የአሜሪካ እየቀነሰ ባለበት በዚህ ወቅት፤ የአፍሪካ ሥራ ፈጣሪዎች በጋራ እንዲንቀሳቀሱ ዶከተሩ ጥሪ አቅርበዋል። የአፍሪካ ሀገራትን "በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና የባሕል ቀንበር" ስር የሚያስቀሩ "አሳሳች ዓላማዎች" የሚከተሉ አንዳንድ መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችንም ኮንነዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0