የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የብሪክስ ቁልፍ ትኩረት መሆን አለበት - የሩሲያ ኩባንያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የብሪክስ ቁልፍ ትኩረት መሆን አለበት - የሩሲያ ኩባንያ
የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የብሪክስ ቁልፍ ትኩረት መሆን አለበት - የሩሲያ ኩባንያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.07.2025
ሰብስክራይብ

የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የብሪክስ ቁልፍ ትኩረት መሆን አለበት - የሩሲያ ኩባንያ

"ዋናው ነገር ማዳበሪያን ጨምሮ የጥሬ ዕቃ ወይም የምርት አቅርቦቶችን መለዋወጥ ብቻ ሳይሆን የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር ጭምር ነው። ይህም በብሪክስ ሀገራት መካከል ጥልቅ ውህደትን ይፈጥራል፤" በማለት የሩሲያ ማዳበሪያ አምራች ፎስ-አግሮ የሽያጭ እና ግብይት ምክትል ኃላፊ ሚካሂል ስተርኪን ተናግረዋል።

ስቴርኪን በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ ከተካሄደው የሩሲያ-ብራዚል የቢዝነስ ፎረም ጎን ለጎን ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ባለፈው ዓመት ፎስ-አግሮ ወደ 4 ሚሊየን ቶን የሚጠጋ ማዕድን ማዳበሪያ ለብሪክስ ገበያዎች ማለትም ለብራዚል፣ ሕንድ እና ደቡብ አፍሪካ ማቅረቡን ገልፀዋል።

"50 በመቶ ምርቶቻችንን ለብሪክስ ገበያዎች እናቀርባለን፡፡ ባለፈው ዓመት 4 ሚሊን ቶን ነበር፤ ዘንድሮ አቅርቦታችንን እንጨምራለን ብዬ አምናለሁ" ብለዋል፡፡

እንደ ምክትል ኃላፊው ገለጻ፤ ሁለቱ ሀገራት ማለትም ብራዚል እና ሩሲያ ባላቸው ከፍተኛ ሳይንሳዊ እምቅ አቅም እና በኢኖቬሽን (በፈጠራዎች) በመታገዝ በግብርና ሥራ ከፍተኛ ውጤቶችን ሊያሳኩ ይችላሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0