ታንዛኒያ ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች አስገዳጅ የ44 ዶላር የጉዞ ዋስትና ይፋ አደረገች
17:51 05.07.2025 (የተሻሻለ: 18:24 05.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ታንዛኒያ ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች አስገዳጅ የ44 ዶላር የጉዞ ዋስትና ይፋ አደረገች
እንደ ሃገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር፤ የጉዞ ኢንሹራንስ ክፍያው (በሀገር ውስጥ ምንዛሬ የሚከፈል)፤ ታንዛኒያ የተጓዦችን ጥበቃ በማጠናከር ራሷን የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ መዳረሻነት ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑን አስታውቋል።
የዋስትና ክፍያው የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
የአደጋ ጊዜ ሕክምና፣
የጠፋ ሻንጣ ካሳ፣
ለአደጋ መታደጊይስ አገልግሎቶች፣
ወደ ሀገር ቤት የመመለሻ ወጪዎች።
ትግበራው በመንግሥት ጋዜጣ ታተሞ የሚወጣ የቁጥጥር መመሪያዎችን ይጠብቃል። ከመቼ እንደሚጀምር ገና አልተረጋገጠም፡፡
የምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ እና የደቡብ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ አባል ሀገራት ዜጎች አዲሱ የዋስትና መስፈርት አይመለከታቸውም።
ፖሊሲው የዛንዚባርን የ2024 የኢንሹራንስ ሞዴል የተከተለ ነው። የቱሪዝም ባለሙያዎች ግን ታንዛኒያን ረግጠው ወደ ዛንዚባር የሚጓዙ ጎብኚዎችን እጥፍ የማስከፈል ስጋት እንዳለ በማንሳት፤ የታንዛኒያን የተዋሃደ የቱሪዝም ብራንድ ሊጎዳ ይችላል የሚል ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X