ኢትዮጵያ አርሶ አደሩን ለማብቃት ያለመ የግብርና መድህን አስጀመረች
16:57 05.07.2025 (የተሻሻለ: 17:04 05.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ አርሶ አደሩን ለማብቃት ያለመ የግብርና መድህን አስጀመረች
ፕሮግራሙ በዘርፉ አርሶ አዳሪው ለቡዙ ግዜ ይገጠመው የነበረውን ተግዳሮት እንደሚቀርፍ ታምኖበታል።
መድህኑ የአርሶ አደሮችን ሕይወት ለመለወጥ፣ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ እና በመላ ሀገሪቱ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር ይረዳል ተብሏል።
በግብርና ሚኒስቴር የገጠር ፋይናንስ አገልግሎት ኃላፊ ጌታቸው መኮንን ስለ ፕሮግራሙ ሲያስረዱ “ይህ የምግብ ደህንነትን ለማሳካት ትልቅ እርምጃ ነው። ተነሳሽነቱን ለማሳደግ እና በአርሶ አደሩ ህይወት ለውጥ ለማምጣት ቁርጠኞች ነን” ማለታቸውን የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ የግብርና ኢንሹራንስ ጥምረት ላይ የተካተቱት ዓባይ ኢንሹራንስ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ፣ ኦሮሚያ ኢንሹራንስ፣ አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አክሲዮን ማኅበር እና የኢትዮጵያ መድኅን ድርጅት ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X