ሩዋንዳ በአሜሪካ አደራዳሪነት ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር የተደረገውን የሰላም ስምምነት አከበራለሁ አለች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩዋንዳ በአሜሪካ አደራዳሪነት ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር የተደረገውን የሰላም ስምምነት አከበራለሁ አለች
ሩዋንዳ በአሜሪካ አደራዳሪነት ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር የተደረገውን የሰላም ስምምነት አከበራለሁ አለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.07.2025
ሰብስክራይብ

ሩዋንዳ በአሜሪካ አደራዳሪነት ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር የተደረገውን የሰላም ስምምነት አከበራለሁ አለች

ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በጎረጎሮሳውያኑ ሰኔ 27 በዋሽንግተን ከተካሄደው ፊርማ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግራቸው፤ የፖለቲካ፣ ጸጥታ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮችን በሚዳስሰው ስምምነት የትራምፕ አስተዳደር ለተጫወተው ሚና በይፋ ምስጋና አቅርበዋል።

ስምምነቱ የተኩስ አቁም እንዲተገበር፣ የኪንሻሳ የግዛት አንድነት ጥያቄ እንዲከበር፣ የታጠቁ ቡድኖች ትጥቅ እንዲፈቱ እና በምስራቅ ኮንጎ መረጋጋት እንዲሰፍን ያስቀምጣል።

ካጋሜ "ስምምነቱን በመተግበር ረገድ መቼም ሩዋንዳን ጥፋተኛ ሆና አታገኟትም"፣ ነገር ግን ሌላኛው ወገን ተንኮልና ችግር የሚፈጥር ከሆነ ያኔ ችግሩን በጄ እንለዋለን ሲሉ ተናግረዋል።

የስምምነቱ ስኬት ቀጣናዊ መልካም ፈቃድን የሚጠይቅ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አፈፃፀሙ በሩዋንዳ እና በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ላይ ብቻ የሚወሰን መሆኑን ነው አጽንዖት የሰጡት።

ስምምነቱ በቅርቡ በኤም23 አማፂ ቡድን ዳግም አገርሽቶ የተጠናከረውን የምስራቅ ኮንጎ ለአስርተ ዓመታት የዘለቀ ብጥብጥ ለማስቆም ያለመ ነው። ኪንሻሳ ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም ቁርጠኛ መሆኗን ቀደም ሲል አረጋግጣለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0