የመከላከያ ምርምር እና ልማት ረቂቅ ፖሊሲ የሰው ሰራሽ አስተውህሎትን ሊያዋህድ እንደሚገባ ተገለፀ
14:11 05.07.2025 (የተሻሻለ: 14:34 05.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የመከላከያ ምርምር እና ልማት ረቂቅ ፖሊሲ የሰው ሰራሽ አስተውህሎትን ሊያዋህድ እንደሚገባ ተገለፀ
የሳይበር ጦርነት አዝማሚዎችን ታሳቢ በማድረግ የቴክኖሎጂ የውጊያ አውዶችን ማየት እንደሚኖርበት ነው የመከላከያ ሠራዊት የትምህርትና ሥልጠና ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮንን አጽንኦት የሰጡት።
ሌተናል ጄኔራል ይመር ረቂቅ ፖሊሲው የኢትዮጵያን የመከላከል አቅም ለማሳደግና ሠራዊቱ የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ የተሻለ ዝግጅት ለማድረግ የላቀ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
የመከላከደ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ የመከላከያ ሠራዊትን ሁለንተናዊ ለውጥ በስኬት መምራት የሚያስችሉ ጥናትና ምርምር ልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በመከላከያ ሚኒስቴር የኢፌዴሪ ዋር ኮሌጅ የብሔራዊ ደኅንነት ኮንፍረንስ፣ የምርምርና ልማት ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ዋና የዘርፉ ተዋናዮች የተሳተፉበት የውይይት መደረጉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X