ትራምፕ "እውነታው እየገባቸው ነው"፤ ስዊዘርላንዳዊው ጋዜጠኛ በቅርቡ በሩሲያ እና በአሜሪካ መሪዎች መካከል ስለተደረገው ውይይት አስተያየታተቸውን ሲሰጡ የተናገሩት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱትራምፕ "እውነታው እየገባቸው ነው"፤ ስዊዘርላንዳዊው ጋዜጠኛ በቅርቡ በሩሲያ እና በአሜሪካ መሪዎች መካከል ስለተደረገው ውይይት አስተያየታተቸውን ሲሰጡ የተናገሩት
ትራምፕ እውነታው እየገባቸው ነው፤ ስዊዘርላንዳዊው ጋዜጠኛ በቅርቡ በሩሲያ እና በአሜሪካ መሪዎች መካከል ስለተደረገው ውይይት አስተያየታተቸውን ሲሰጡ የተናገሩት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.07.2025
ሰብስክራይብ

ትራምፕ "እውነታው እየገባቸው ነው"፤ ስዊዘርላንዳዊው ጋዜጠኛ በቅርቡ በሩሲያ እና በአሜሪካ መሪዎች መካከል ስለተደረገው ውይይት አስተያየታተቸውን ሲሰጡ የተናገሩት

ከፑቲን ጋር በነበራቸው ውይይት "ደስተኛ እንዳልሆኑ" የገለፁት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት፤ የዩክሬንን ጉዳይ ለመፍታት "ወራት ምናልባትም ዓመታት" እንደሚወስድ መረዳት ጀምረዋል ሲሉ ጋይ ሜታን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ነገር ግን ታሪክ እንደሚያሳየው በትልልቅ ድርድሮች መሻሻል ከመታየቱ በፊት የሚፈጥንበት እንዲሁም የሚቆምበት ሂደት ይኖራል፡፡

ሜታን አሜሪካ ወደ ኪዬቭ የምትልከውን የጦር መሣሪያ ማቆሟን በተመለከተ ሲናገሩ፤ ትራምፕ "የዩክሬን ጦርነት ኃላፊነትን ወደ አውሮፓውያን ማሸጋገር" እንደሚፈልጉ ጠቁሟል።

"ይህ አውሮፓ ለዩክሬን የምታቀርበውን የጦር መሣሪያ ከአሜሪካ ትገዛለች ማለት ነው፡፡ ይህን ከጨዋታ ውጪ ማድረግ አንችልም" ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ ምዕራባውያን ቀስ በቀስ የጦር መሣሪያ እና ጥይቶች እጥረት እንደሚገጥማቸው ተንታኙ አስጠንቅቀዋል።

ቢሆንም የጦርነት ሂደቱ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል እምነታቸውን ገልፀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0