ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግብይት ከሞላ ጎደል ወደ ሩብል እየቀየረች ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግብይት ከሞላ ጎደል ወደ ሩብል እየቀየረች ነው
ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግብይት ከሞላ ጎደል ወደ ሩብል እየቀየረች ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.07.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግብይት ከሞላ ጎደል ወደ ሩብል እየቀየረች ነው

ሩሲያ በመገበያያ ገንዘቧ ለአፍሪካ ሀገራት የምትልከው ምርት ድርሻ 98.3 በመቶ ደርሷል፡፡ ባለፈው ወር ብቻ የ8 በመቶ ጭማሪ አለው፡፡ ከዓመት በፊት ከነበረበት 60.5% አንጻር ጉልህ እድገት ማሳየቱን የሩሲያ ሚዲያዎች አስለትውታል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት የሩሲያ ሸቀጦችን ለመሸመት ሩብልን ይገዛሉ፡፡ በተለይም ሩብል ከማግኘታቸው በፊት ብሔራዊ ገንዘባቸውን ወደ ዶላር እንደሚቀይሩ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አንድሬ ባርክሆታ አስረድተዋል፡፡

ይህ ውጤት በማዕቀብ ውስጥ የምትገኘው ሩሲያ "መርዛማ ወዳልሆኑ" መገበያያ ገንዘቦች ፊቷን በማዞሯ የመጣ ነው። በአጠቃላይ የውጭ ንግድ ውስጥ የሩብል አገልግሎት ከ52% ተሻግሯል፡፡ በተለይም በብሪክስ እና በዩሬዥያ ኢኮኖሚ ሕብረት፤ ለአብነትም ከግብጽ ጋር 40 በመቶ የሚሆነው ግብይት በብሔራዊ መገበያያ ገንዘብ ተደርጓል፡፡

ባርክሆታ የሩብል ክፍያዎች የአይነት ልውውጥ መሰል ንግዶች ውስጥ ያለውን የተጣራ መጠን ብቻ ሊሸፍኑ እንደሚችሉ ይጠቁማሉ። ሩሲያ በዩራኒየም እና በኮኮዋ ፍሬ ምትክ የምህንድስና ምርቶችን በማቅረብ ልዩነቱን በሩብል መለዋወጥ ትችላለች።

የአፍሪካን እያደገ የንግድ ሚና ግምት ውስጥ በማስገባት ከ2030 እስከ 2032 በዓለም አቀፍ የገንዘብ ልውውጥ ውስጥ የሩብል መጠን 0.7 እስከ 1% ሊደርስ እንደሚችል የተነበዩት የፋይናንስ ተንታኝ ናታልያ ሚልቻኮቫ ናቸው። ይህ መቶኛ ትንሽ ቢመስልም የዓለም መጠባበቂያ ገንዘብ ቁመና ኖሮት ከ5% በታች የሚገኘውን የዩዋንን ድርሻ ተቃርቧል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0