ኒጀር ከ265 ሺህ ሄክታር በላይ የተራቆተ መሬት ወደነበረበት ለመመለስ ወጥናለች
19:59 04.07.2025 (የተሻሻለ: 20:04 04.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኒጀር ከ265 ሺህ ሄክታር በላይ የተራቆተ መሬት ወደነበረበት ለመመለስ ወጥናለች
ሀገሪቱ የግብርና ልማት አቅምን ለማጠናከር ከ30.5 ሚሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አግኝታለች።
ለዚህም ኒጄር እና የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ሐሙስ በይፋ ስምምነት አድርገዋል።
“በአፍሪካ ታላቁ አረንጓዴ ግንብ ዘላቂነትን ማሳደግ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ፕሮጀክት በዙ ቁልፍ ዓላማዎች አሉት፡-
🟠 መሬት ማልማት፣
🟠 ከ700 በላይ ማኀበረሰብ አቀፍ የችግኝ ጣቢዎችን መፍጠር፣
🟠 በመልሶ ማቋቋም እና በዘላቂ የተፈጥሮ ሃብት አስተዳደር ከ1 ሺሀ በላይ የሀገር ውስጥ ቡድኖችን ማሠልጠን፣
🟠 የበካይ ጋዝ (ካርብን ዳይኦክሳይድ) ልቀትን በከፍተኛ መቀነስ።
ፕሮጀክቱ የፓን-አፍሪካ ታላቁ አረንጓዴ ግንብ መርሃ-ግብር አካል ነው፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X