- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

የኢትዮጵያን ዕምቅ የማዕድን ሐብትን የመረዳት እውነታ፦ ከሩሲያ ጋር ያለ ስልታዊ አጋርነት

የኢትዮጵያን ዕምቅ የማዕድን ሐብትን የመረዳት እውነታ፦ ከሩሲያ ጋር ያለ ስልታዊ አጋርነት
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ የማዕድን ሀብቶች አላት ፤ ከእነዚህም መካከል ወርቅ፣ ታንታለም፣ ሊቲየም እና ሌሎቹ በምድሯ ይዛለች።
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ትናንት ለምክርቤት አባላት ማብራሪያ ሲሰጡ ማዕድንን በተመለከተ "ኢትዮጵያ ከፍተኛ ማዕድን ሀብት ያላት ሀገር ናት [...] ዘንድሮ ከወርቅ ብቻ [አምና ከነበረው በ10 እጥፍ ዕድገት] 3.5 ቢሊየን ዶላር ከዉጪ ንግድ አግኝተናል" ብለዋል።
የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ማዕድን እና ጂኦሎጂካል ሀብት ፍለጋ ከሩሲያ ጋር ስላለው ስትራቴጂያዊ ትብብርና ሌሎች ተያያዥ ሀሳቦች በጥልቀት ለመወያየት ዶ/ር በቀለ አየለ በዳዳ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ጂኦሎጂ ዲፓርትመንት ረዳት ፕሮፌሰር እንዲሁም በማዕድን ዘርፎች አማካሪ ሙስጠፋ ሻይኮ ሼኩን ጋብዟቸዋል።
በኢትዮጵያ ስለሚገኘው እምቅ የተፈጥሮ ማዕድን በተመለከተ የዘርፉ ምሁር ዶ/ር በቀለ ሲያስረዱ፦
“ከምጣኔ ሀብታዊ ማሻሻያ ጋር የተያያዙ ብዙ ስትራተጂያዊ ማዕድናት አሉን። ማዕድናቱ በአብዛኛው በደቡብ፣ በምዕራብ እና በሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል የተሰራጩ ናቸው። ስለዚህ እነዚያን ማዕድናት በዘላቂነት
በዘርፉ ከሩሲያ ጋር የሚፈጠሩ ትብብሮችና አጋርነቶች ስለሰጡት ፋይዳዎች የዘርፉ አማካሪ ሙስጠፋ ሲያብራሩ፦
"የላቀ ቴክኖሎጂ አላቸው። ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር በመሥራቷ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ ናት። ስለዚህ ትብብሩ ከሩሲያ ወደ ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚፈጥር ይመስለኛል - ብዙ የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎች እንደመኖራቸው፣" ሲሉ ተናግረዋል።
በተግባር የሚገለፁ ትብብሮች ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ያራምዳሉ ፤ መጠነ ሰፊ መዋዕለ ንዋዮች ደግሞ ኢትዮጵያን ወደ ልማት ግቦቿ የበለጠ ያስጠጓታል።
የበለጠ ለመረዳት በዚሁ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ማዕድን እና ጂኦሎጂካል ሀብት ፍለጋ እንዲሁም ፈተናዎቹ የተዳሰሱበትን ዝግጅት ይከታተሉ!
ለማድመጥ ዝግጁ ነዎት?
አዳዲስ ዜናዎች
0