የሩሲያ ኬሚካል ሆልዲንግ በ2024 ለብሪክስ ሀገራት 4 ሚሊየን ቶን ማዳበሪያ አቀረበ
17:14 04.07.2025 (የተሻሻለ: 17:34 04.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኬሚካል ሆልዲንግ በ2024 ለብሪክስ ሀገራት 4 ሚሊየን ቶን ማዳበሪያ አቀረበ
ከዓለም ቀዳሚ የፎስፈረስ ይዘት ማዳበሪያ አምራች ከሆኑት ውስጥ አንዱ ፎስአግሮ፤ በተለይም ለብራዚል፣ ሕንድ እና ደቡብ አፍሪካ በቀዳሚነት ምርቱን እንዳቀረበ የኩባንያው የሽያጭ፣ ግብይት እና ሎጅስቲክስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚካሂል ስተርኪን ተናግረዋል፡፡
ሰተርኪን የአውሮፓ ሕብረት በሩሲያ ማዳበሪያ ላይ ወደፊት ሊጥላቸው የሚችሉ ቀረጦችን በመጠቆም፤ ሩሲያ አቅርቦቷን ፍላጎት ላሳዩ ሀገራት እንደምታዞር ገልፀዋል፡፡ በሪዮ ዴጄኔሮ ከተካሄደው የሩሲያ-ብራዚል የቢዝነስ ፎረም ጎን ለጎን የሩሲያ ማዳበሪያ የላቀ ጥራት እንዳለውም አፅንዖት ሰጠተዋል።
አውሮፓ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ ያልሆኑ እና ዝቅተኛ ጥራት ያላቸውን አማራጮች ከሌሎች አቅራቢዎች ለመፈለግ እንደምትገደድም ተንብየዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X