“ኔቶ ይህን ጦርነት በሩስያ ተሸንፏል እናም አስፈላጊ መቋጫ ለመስጠት ጊዜው አሁን ነው”

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ“ኔቶ ይህን ጦርነት በሩስያ ተሸንፏል እናም አስፈላጊ መቋጫ ለመስጠት ጊዜው አሁን ነው”
“ኔቶ ይህን ጦርነት በሩስያ ተሸንፏል እናም አስፈላጊ መቋጫ ለመስጠት ጊዜው አሁን ነው” - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.07.2025
ሰብስክራይብ

“ኔቶ ይህን ጦርነት በሩስያ ተሸንፏል እናም አስፈላጊ መቋጫ ለመስጠት ጊዜው አሁን ነው”

"ዶናልድ ትራምፕ ይህ ጦርነት እንዲያበቃ የሚሹ ይመስለኛል። የሩሲያን ጥቅም በወጉ ሳይረዱ አየቀርም፡፡ የተለመዱ ስትራቴጂካዊ ፍላጎቶች ማለቴ ነው፤" ሲሉ ጡረተኛው ፈረንሳዊ ኮሎኔል ዣክ ሆጋርድ አሜሪካ ወደ ኪዬቭ የምታደርሰውን የጦር መሣሪያ ድጋፍ ማቋረጧን አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

እሳቸው እንደሚሉት “ይህ በእውነቱ ለዶናልድ ትራምፕ ያሸነፈ አመክንዮ ነው።" ከአሁን በኋላ ትራምፕ "እስካሁን የሆነው እንደሚበቃ ይገነዘቡ ዘንድ ዜለንስኪ ላይ ጫና ያሳድራሉ፡፡"

"ይህ ግጭት በጣም ውድ ነው፤ አሜሪካም በቅቷታል፡፡ የአውሮፓ ሕብረት እና የኔቶ ሀገራት የሩሲያ ወታደራዊ ግስጋሴ ላይ መድረስ የሚችሉበት መንገድ የላቸውም” ሲሉ የቀድሞው መኮንን አጽንኦት ሰጥተዋል።

የምዕራባውያን መሪዎች በሩሲያ ላይ ለዘብ ያለ እርምጃ እየተከተሉ መሆኑንም ጠቁመዋል።

"መፍትሄ መገኘት እንዳለበት ለራሳቸው እየነገሩ ነው፤ ይህ መፍትሄ ደግሞ ዩክሬንን የሚጎዳ መሆኑ የማይቀር ነው" ሲሉ ሆጋርድ አበክረው ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0