የኢትዮጵያውያን አይሁዶች ጥንታዊ መጻሕፍት ተገኙ
15:10 04.07.2025 (የተሻሻለ: 15:34 04.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያውያን አይሁዶች ጥንታዊ መጻሕፍት ተገኙ
የቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሁለት ቅዱሳት ጽሑፎችን አግኝተዋል፡፡ ግኝቶቹ የኢትዮጵያ አይሁድ ማኅበረሰብ (ቤተ-እስራኤላውያን) ጥንታዊ ሐይማኖታዊ ጽሕፈት ያደርጋቸዋል፡፡
የተገኙት የብራና መጻሕፍት፦
የኦሪት ጥቅሎች የሚባሉት እነዚህ መጻሕፍቶች አምስቱን የሙሴ መጻሕፍት ጨምሮ መጽሐፈ ኢያሱ፣ መጽሐፈ መሳፍንት እና መጽሐፈ ሩትን ያካትታሉ፣
በጥንታዊው የኢትዮጵያ ቋንቋ ግዕዝ የተጻፉ ናቸው፡፡
ጥቅሎቹ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉና በጥብቅ ይጠበቁ የነበሩ ናቸው። አንዳንድ የመጽሕፍቱ ባለቤቶች ወደ እስራኤል ለመውሰድ ሕይወታቸውን ጭምር አደጋ ላይ ጥለው ነበር ተብሏል።
መሰል ጥንታዊ የአይሁድ ጽሑፎች በቤተ እስራኤላውያን ዘንድ መኖራቸው ሲረጋገጥ ይህ የመጀመሪያው ነው።
ግኝቱ የቤተ እስራኤላውያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወጎች ለመመዝገብ፣ ለማጥናት እና ለመጠበቅ የሚደረገው ሰፊ ጥረት አካል ነው። ተመራማሪዎች ፈጽሞ ያልተጻፈውን የቀሳውስት የቃል ትምህርቶች እና ትርጓሜዎችን ለመመዝገብ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ የሰለጠኑ 18 ቀሳውስት ብቻ እስከ ዛሬ ድረስ ይህንን እውቀት ይዘው ይገኛሉ።
የብራናዎቹ ፎቶዎች፡ ቴድ ኤርሆ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
