የሩሲያ እና ኢትዮጵያ ባሕሎችን በጥበብ ያስተሳሰርው አርቲስት ቴዎድሮስ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ እና ኢትዮጵያ ባሕሎችን በጥበብ ያስተሳሰርው አርቲስት ቴዎድሮስ

አርቲስት ቴዎድሮስ አበባው ሴንት ፒተርስበርግ ከሚገኘው የሪፒን የጥበብ አካዳሚ በስኬት ተመርቋል፡፡

“ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፡ የ1888 ዓ.ም የዓድዋ የነፃነት ትግል አዋጅ” ብሎ የሰየመውን የመመረቂያ የሥዕል ሥራ አቅርቧል፡፡ ሥራው በአርቲስት አሌክሳንደር ክሪሎቭ አጋዥነት የተጠናቀቀ ነው፡፡

ቴዎድሮስ አዲስ አበባ በሚገኘው የፖሊቴክኒክ ኢንስቲትዩት ከመማር ተነስቶ ወደ ሥመ-ጥሩ የሩሲያ የአካዳሚክ ሥዕል ትምህርት ቤት ጠቢብነት ሙያውን አሸጋግሯል። በሥራዎቹ የኢትዮጵያን ቅርሶች ከጥንታዊ የጥበብ ስልቶች ጋር በጥበብ ማዛመድ ችሏል።

የቅርብ ጊዜ ስኬቶቹ፦

የ "ዩናይትድ ታለንት 2024" ውድድር ("ከአፍሪካ እይታ" ምድብ) አሸናፊ፣

የሞስኮ እና ሴንት ፒተርስበርግ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ተሳትፎ፡፡

የቴዎድሮስ ሥራዎች በባሕሎች መካከል ለሚደረገው ውይይት ልዩ ትኩረት ይሰጣሉ። በባሕል፣ በታሪክ፣ በወግ እና በመንፈሳዊ እሴቶች ውስጥ የጋራ ባህሪያትን በማገናኘት በሩሲያ እና በኢትዮጵያ ባሕሎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሳየት ይተጋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ እና ኢትዮጵያ ባሕሎችን በጥበብ ያስተሳሰርው አርቲስት ቴዎድሮስ
የሩሲያ እና ኢትዮጵያ ባሕሎችን በጥበብ ያስተሳሰርው አርቲስት ቴዎድሮስ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.07.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0