የቻይና የሕክምና ቡድን ለጥሩነሽ-ቤጂንግ ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
14:35 04.07.2025 (የተሻሻለ: 14:54 04.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቻይና የሕክምና ቡድን ለጥሩነሽ-ቤጂንግ ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
እርዳታው በዚህ ዓመት ብቻ ለሆስፒታሉ ለሦስተኛ ጊዜ ሲደረግ እንደሆነ በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተጠቁሟል፡፡
የጥሩነሽ-ቤጂንግ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እሸቱ ታደለ "በኢትዮጵያ ያለውን የጤና ሥርዓት የሚያጠናክር የሰው ኃይል፣ የሕክምና መሣሪያ እና የክህሎት ሽግግር ስላደረጋችሁልን እናመሰናለን" ሲሉ መናገራቸውን ሺንዋ ዘግቧል፡፡
የቻይና ሐኪሞች አገልግሎት የሁለቱ ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር በጉልህ የሚታይበት መሆኑንም አስምረውበታል።
"ከሀገር ውስጥ የሕክምና ባለሙያዎች ጋር ልምዳቸውን ከማጋራት ጎን ለጎን፤ በቀጣይም ቻይና የሕክምና ቡድኖችን በመላክ ሕክምና ለሚሹ ኢትዮጵያውያን የጤና አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ ናት" ያሉት በኢትዮጵያ 25ኛው የቻይና የሕክምና ቡድን መሪ ሊዩ ጁንዪንግ ናቸው፡፡
የቻይና የሕክምና ቡድን በሀገሪቱ ከ1970ዎቹ ጀምሮ የተለያዩ የሕክምና አገልግሎቶችን መስጠቱን የቀጠለ ሲሆን 16 ስፔሻሊስቶችን ያቀፈው 26ኛው የቻይና የህክምና ቡድን ለአንድ ዓመት የሚቆየውን የበጎ አድራጎት ለመጀመር አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
